-
ዕዝራ 7:21-24አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
21 “እኔ ንጉሥ አርጤክስስ ከወንዙ ባሻገር* ባለው ክልል የምትገኙትን የግምጃ ቤት ኃላፊዎች በሙሉ የሰማይ አምላክ ሕግ ገልባጭ* የሆነው ካህኑ ዕዝራ+ የጠየቃችሁን ነገር ሁሉ በአስቸኳይ እንድትፈጽሙለት ትእዛዝ ሰጥቻለሁ፤ 22 እንዲሁም እስከ 100 ታላንት* ብር፣ እስከ 100 የቆሮስ* መስፈሪያ ስንዴ፣ እስከ 100 የባዶስ* መስፈሪያ የወይን ጠጅና+ እስከ 100 የባዶስ መስፈሪያ ዘይት+ ድረስ ስጡት፤ እንዲሁም የፈለገውን ያህል ጨው+ ስጡት። 23 በንጉሡ ግዛትና በልጆቹ ላይ ቁጣ እንዳይወርድ+ የሰማይ አምላክ፣ የሰማይን አምላክ ቤት አስመልክቶ ያዘዘው ሁሉ በትጋት ይፈጸም።+ 24 በተጨማሪም ከካህናቱ፣ ከሌዋውያኑ፣ ከሙዚቀኞቹ፣+ ከበር ጠባቂዎቹ፣ ከቤተ መቅደስ አገልጋዮቹም*+ ሆነ ይህን የአምላክ ቤት ከሚሠሩት ሰዎች መካከል በአንዳቸውም ላይ ምንም ዓይነት ቀረጥ፣ ግብር+ ወይም የኬላ ቀረጥ መጣል እንደማትችሉ እወቁ።
-