1 ዜና መዋዕል 16:4 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 4 ከዚያም የእስራኤልን አምላክ ይሖዋን ያከብሩ፣* ያመሰግኑና ያወድሱ ዘንድ የተወሰኑ ሌዋውያንን በይሖዋ ታቦት ፊት እንዲያገለግሉ ሾመ።+ 1 ዜና መዋዕል 23:28 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 28 የሌዋውያኑ ተግባር በይሖዋ ቤት አገልግሎት የሚከናወነውን ሥራ ይኸውም ቅጥር ግቢዎቹንና+ የመመገቢያ ክፍሎቹን፣ ቅዱስ የሆነውን ነገር ሁሉ የማንጻቱን ሥራና በእውነተኛው አምላክ ቤት የሚከናወኑትን አስፈላጊ ሥራዎች ሁሉ ኃላፊነት ወስደው በመሥራት የአሮንን ልጆች+ መርዳት ነበር። 1 ዜና መዋዕል 23:30 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 30 ለይሖዋ ምስጋናና ውዳሴ ለማቅረብ ጠዋት ጠዋትም+ ሆነ ማታ ማታ+ ይቆሙ ነበር።
28 የሌዋውያኑ ተግባር በይሖዋ ቤት አገልግሎት የሚከናወነውን ሥራ ይኸውም ቅጥር ግቢዎቹንና+ የመመገቢያ ክፍሎቹን፣ ቅዱስ የሆነውን ነገር ሁሉ የማንጻቱን ሥራና በእውነተኛው አምላክ ቤት የሚከናወኑትን አስፈላጊ ሥራዎች ሁሉ ኃላፊነት ወስደው በመሥራት የአሮንን ልጆች+ መርዳት ነበር።