25 በተጨማሪም ዳዊትና የአገልግሎት ቡድኖቹ አለቆች በበገና፣ በባለ አውታር መሣሪያዎችና+ በሲምባል+ ትንቢት በመናገር እንዲያገለግሉ ከአሳፍ፣ ከሄማን እና ከየዱቱን+ ወንዶች ልጆች መካከል አንዳንዶቹን ለዩ። ይህን አገልግሎት የሚያከናውኑት ኃላፊነት ያላቸው ሰዎች ዝርዝር የሚከተለው ነው፦ 2 ከአሳፍ ወንዶች ልጆች መካከል ዛኩር፣ ዮሴፍ፣ ነታንያህ እና አሼርዔላ፤ እነዚህ በአሳፍ አመራር ሥር ያሉ የአሳፍ ወንዶች ልጆች ሲሆኑ በንጉሡ አመራር ሥር ሆነው ትንቢት ይናገሩ ነበር።