12 የይሁዳ ሰዎችም ሁሉ የእህሉን፣ የአዲሱን የወይን ጠጅና የዘይቱን አንድ አሥረኛ+ ወደ ግምጃ ቤቶቹ አስገቡ።+ 13 ከዚያም ካህኑን ሸሌምያህን፣ የቅዱሳን መጻሕፍት ገልባጭ የሆነውን ሳዶቅን እንዲሁም ከሌዋውያን መካከል ፐዳያህን በግምጃ ቤቶቹ ላይ ኃላፊዎች አደረግኳቸው፤ የማታንያህ ልጅ፣ የዛኩር ልጅ ሃናን ደግሞ የእነሱ ረዳት ነበር፤ እነዚህ ሰዎች እምነት የሚጣልባቸው ነበሩ። ለወንድሞቻቸው የማከፋፈሉ ኃላፊነት የእነሱ ነበር።