-
አስቴር 4:1-3አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
4 መርዶክዮስ+ የተደረገውን ነገር ሁሉ ባወቀ ጊዜ+ ልብሱን ቀደደ፤ ማቅም ለበሰ፤ በራሱም ላይ አመድ ነሰነሰ። ከዚያም ድምፁን ከፍ አድርጎ እየጮኸና ምርር ብሎ እያለቀሰ ወደ ከተማዋ መሃል ወጣ። 2 ማንም ሰው ማቅ ለብሶ በንጉሡ በር እንዲገባ ስለማይፈቀድለት እስከ ንጉሡ በር ድረስ መጣ። 3 የንጉሡ ቃልና ድንጋጌ በተሰማባቸው አውራጃዎች በሙሉ+ በሚገኙ አይሁዳውያን መካከል ታላቅ ሐዘን ሆነ፤ እነሱም ጾሙ፤+ አለቀሱ፤ እንዲሁም ዋይታ አሰሙ። ብዙዎቹ ማቅ አንጥፈው፣ አመድ ነስንሰው ተኙ።+
-