ዘኁልቁ 16:22 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 22 እነሱም በግንባራቸው መሬት ላይ ተደፍተው እንዲህ አሉ፦ “አምላክ ሆይ፣ አንተ የሰው ሁሉ መንፈስ* አምላክ ነህ፤+ ታዲያ አንድ ሰው በሠራው ኃጢአት የተነሳ በመላው ማኅበረሰብ ላይ ትቆጣለህ?”+ መዝሙር 104:30 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 30 መንፈስህን ከላክ ይፈጠራሉ፤+የምድርንም ገጽ ታድሳለህ። መክብብ 12:7 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 7 አፈር ቀድሞ ወደነበረበት መሬት ይመለሳል፤+ መንፈስም* ወደ ሰጪው፣ ወደ እውነተኛው አምላክ ይመለሳል።+ ሕዝቅኤል 18:4 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 4 እነሆ፣ ነፍስ* ሁሉ የእኔ ነው። የአባት ነፍስ የእኔ እንደሆነች ሁሉ የልጅም ነፍስ የእኔ ናት። ኃጢአት የምትሠራ ነፍስ እሷ ትሞታለች።*
22 እነሱም በግንባራቸው መሬት ላይ ተደፍተው እንዲህ አሉ፦ “አምላክ ሆይ፣ አንተ የሰው ሁሉ መንፈስ* አምላክ ነህ፤+ ታዲያ አንድ ሰው በሠራው ኃጢአት የተነሳ በመላው ማኅበረሰብ ላይ ትቆጣለህ?”+