ኢዮብ 12:6 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 6 የዘራፊዎች ድንኳን ሰላም አለው፤+አምላክን የሚያስቆጡ ሰዎችም፣አምላካቸውን* በእጃቸው እንደያዙ ሰዎች የደህንነት ስሜት ይሰማቸዋል።+ መዝሙር 37:7 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 7 በይሖዋ ፊት ዝም በል፤+እሱንም በተስፋ* ተጠባበቅ። የጠነሰሰውን ሴራበተሳካ ሁኔታ እየፈጸመ ባለ ሰው አትበሳጭ።+ መዝሙር 73:3 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 3 ክፉ ሰዎች ያላቸውን ሰላም በተመለከትኩ ጊዜ፣እብሪተኛ በሆኑ ሰዎች* ቀንቼ ነበርና።+ መዝሙር 73:12 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 12 አዎ፣ ክፉዎች እንደዚህ ናቸው፤ ሁልጊዜ ሳይጨናነቁ ይኖራሉ።+ የሀብታቸውንም መጠን ያሳድጋሉ።+ ኤርምያስ 12:1 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 12 ይሖዋ ሆይ፣ አቤቱታዬን ለአንተ ሳቀርብ፣ከፍትሕ ጋር ስለተያያዙ ጉዳዮች ሳናግርህ እነሆ፣ አንተ ጻድቅ ነህ።+ ታዲያ የክፉዎች መንገድ ለምን ይሰምራል?+ደግሞስ ከዳተኞች ሳይጨነቁ የሚኖሩት ለምንድን ነው?
12 ይሖዋ ሆይ፣ አቤቱታዬን ለአንተ ሳቀርብ፣ከፍትሕ ጋር ስለተያያዙ ጉዳዮች ሳናግርህ እነሆ፣ አንተ ጻድቅ ነህ።+ ታዲያ የክፉዎች መንገድ ለምን ይሰምራል?+ደግሞስ ከዳተኞች ሳይጨነቁ የሚኖሩት ለምንድን ነው?