-
ዘኁልቁ 12:14አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
14 ይሖዋም ሙሴን እንዲህ አለው፦ “አባቷ ፊቷ ላይ ቢተፋባት ለሰባት ቀን ተዋርዳ ትቆይ አልነበረም? አሁንም ከሰፈር ውጭ ለሰባት ቀን ተገልላ እንድትቆይ ይደረግ፤+ ከዚያ በኋላ እንድትመለስ ማድረግ ይቻላል።”
-
-
ዘዳግም 25:9አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
9 የወንድሙ ሚስት በሽማግሌዎቹ ፊት ወደ እሱ ቀርባ ጫማውን ከእግሩ ላይ ታውልቅ፤+ ከዚያም ፊቱ ላይ ትትፋበትና ‘የወንድሙን ቤት በማይሠራ ሰው ላይ የሚደረግበት እንዲህ ነው’ ትበል።
-
-
ኢሳይያስ 50:6አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
6 ለሚገርፉኝ ጀርባዬን፣
ጢም ለሚነጩም ጉንጮቼን ሰጠሁ።
ፊቴን፣ ከሚያዋርዱ ነገሮችና ከትፋት አልሰወርኩም።+
-
-
ማቴዎስ 27:30አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
30 ደግሞም ተፉበት፤+ መቃውንም ወስደው ራሱን ይመቱት ጀመር።
-