ዘፍጥረት 2:7 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 7 ይሖዋ አምላክም ሰውን ከምድር አፈር ሠራው፤+ በአፍንጫውም የሕይወትን እስትንፋስ እፍ አለበት፤+ ሰውየውም ሕያው ሰው* ሆነ።+ መክብብ 12:7 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 7 አፈር ቀድሞ ወደነበረበት መሬት ይመለሳል፤+ መንፈስም* ወደ ሰጪው፣ ወደ እውነተኛው አምላክ ይመለሳል።+ የሐዋርያት ሥራ 17:25 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 25 በተጨማሪም ሕይወትንና እስትንፋስንም ሆነ ማንኛውንም ነገር ለሰው ሁሉ የሚሰጠው+ እሱ ስለሆነ የሚጎድለው ነገር ያለ ይመስል በሰው እጅ አይገለገልም።+