መዝሙር 89:14 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 14 ጽድቅና ፍትሕ የዙፋንህ መሠረት ናቸው፤+ታማኝ ፍቅርና ታማኝነት በፊትህ ናቸው።+ መዝሙር 97:2 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 2 ደመናና ድቅድቅ ጨለማ በዙሪያው አለ፤+ጽድቅና ፍትሕ የዙፋኑ መሠረት ናቸው።+ መዝሙር 99:4 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 4 እሱ ፍትሕን የሚወድ ኃያል ንጉሥ ነው።+ አንተ ቅን የሆነውን ነገር በጽኑ መሥርተሃል። ፍትሕንና ጽድቅን ለያዕቆብ አስፍነሃል።+ ሮም 2:11 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 11 በአምላክ ዘንድ አድልዎ የለምና።+