ዘፀአት 22:28 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 28 “አምላክን አትራገም፤+ በሕዝብህ መካከል ያለውን አለቃም* አትራገም።+ መክብብ 8:2-4 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 2 እኔም እንዲህ እላለሁ፦ “በአምላክ ፊት በገባኸው መሐላ+ የተነሳ የንጉሥን ትእዛዝ አክብር።+ 3 ከንጉሡ ፊት ለመውጣት አትቸኩል።+ መጥፎ የሆነውን ነገር ሁሉ አትደግፍ፤+ እሱ ደስ ያሰኘውን ሁሉ ማድረግ ይችላልና፤ 4 ምክንያቱም የንጉሥ ቃል የማይሻር ነው፤+ ‘ምን ማድረግህ ነው?’ ሊለው የሚችል ማን ነው?” መክብብ 10:20 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 20 በሐሳብህ* እንኳ ንጉሡን አትርገም፤*+ በመኝታ ቤትህም ሆነህ ባለጸጋውን አትርገም፤ ቃሉን* ወፍ* ልትወስደው አሊያም ክንፍ ያላት ፍጥረት የተወራውን ደግማ ልትናገር ትችላለችና።
2 እኔም እንዲህ እላለሁ፦ “በአምላክ ፊት በገባኸው መሐላ+ የተነሳ የንጉሥን ትእዛዝ አክብር።+ 3 ከንጉሡ ፊት ለመውጣት አትቸኩል።+ መጥፎ የሆነውን ነገር ሁሉ አትደግፍ፤+ እሱ ደስ ያሰኘውን ሁሉ ማድረግ ይችላልና፤ 4 ምክንያቱም የንጉሥ ቃል የማይሻር ነው፤+ ‘ምን ማድረግህ ነው?’ ሊለው የሚችል ማን ነው?”
20 በሐሳብህ* እንኳ ንጉሡን አትርገም፤*+ በመኝታ ቤትህም ሆነህ ባለጸጋውን አትርገም፤ ቃሉን* ወፍ* ልትወስደው አሊያም ክንፍ ያላት ፍጥረት የተወራውን ደግማ ልትናገር ትችላለችና።