መዝሙር 24:8 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 8 ይህ ክብር የተጎናጸፈ ንጉሥ ማን ነው? ብርቱና ኃያል የሆነው ይሖዋ ነው፤+በውጊያ ኃያል የሆነው ይሖዋ ነው።+ መዝሙር 99:4 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 4 እሱ ፍትሕን የሚወድ ኃያል ንጉሥ ነው።+ አንተ ቅን የሆነውን ነገር በጽኑ መሥርተሃል። ፍትሕንና ጽድቅን ለያዕቆብ አስፍነሃል።+ ኤርምያስ 32:18 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 18 ለሺዎች ታማኝ ፍቅር ታሳያለህ፤ ይሁንና የአባቶችን በደል ከእነሱ በኋላ በሚመጡት ልጆቻቸው ላይ* ትመልሳለህ፤+ አንተ እውነተኛ፣ ታላቅና ኃያል አምላክ ነህ፤ ስምህም የሠራዊት ጌታ ይሖዋ ነው።
18 ለሺዎች ታማኝ ፍቅር ታሳያለህ፤ ይሁንና የአባቶችን በደል ከእነሱ በኋላ በሚመጡት ልጆቻቸው ላይ* ትመልሳለህ፤+ አንተ እውነተኛ፣ ታላቅና ኃያል አምላክ ነህ፤ ስምህም የሠራዊት ጌታ ይሖዋ ነው።