-
ዘፀአት 9:23አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
23 በመሆኑም ሙሴ በትሩን ወደ ሰማይ አነሳ፤ ይሖዋም ነጎድጓድና በረዶ ላከ፤ እሳትም* በምድር ላይ ወረደ፤ ይሖዋ በግብፅ ምድር ላይ ያለማቋረጥ በረዶ እንዲወርድ አደረገ።
-
-
1 ሳሙኤል 12:17, 18አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
17 ዛሬ የስንዴ መከር የሚታጨድበት ጊዜ አይደለም? ይሖዋን ነጎድጓድና ዝናብ እንዲልክ እጠይቀዋለሁ፤ እናንተም ንጉሥ እንዲነግሥላችሁ በመጠየቅ በይሖዋ ፊት ምን ያህል ታላቅ በደል እንደፈጸማችሁ ታውቃላችሁ፤ ደግሞም ታስተውላላችሁ።”+
18 ከዚያም ሳሙኤል ይሖዋን ጠየቀ፤ ይሖዋም በዚያ ቀን ነጎድጓድና ዝናብ ላከ፤ በመሆኑም ሕዝቡ ሁሉ ይሖዋንና ሳሙኤልን እጅግ ፈራ።
-