ዘፍጥረት 6:2 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 2 የእውነተኛው አምላክ ልጆችም*+ የሰዎች ሴቶች ልጆች ውብ እንደሆኑ አስተዋሉ። በመሆኑም የመረጧቸውን ሁሉ ለራሳቸው ሚስቶች አድርገው ወሰዱ። 1 ነገሥት 22:19 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 19 በዚህ ጊዜ ሚካያህ እንዲህ አለ፦ “እንግዲህ የይሖዋን ቃል ስማ፦ ይሖዋ በዙፋኑ ላይ ተቀምጦ+ የሰማያት ሠራዊትም ሁሉ በቀኙና በግራው አጠገቡ ቆመው+ አየሁ። ኢዮብ 1:6 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ ኢዮብ 2:1 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 2 የእውነተኛው አምላክ ልጆች፣*+ በይሖዋ ፊት ለመቆም+ የሚገቡበት ቀን በደረሰ ጊዜ ሰይጣንም በይሖዋ ፊት ለመቆም እነሱ መካከል ገባ።+ መዝሙር 89:6 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 6 በሰማያት ከይሖዋ ጋር ማን ሊወዳደር ይችላል?+ ከአምላክ ልጆች*+ መካከል እንደ ይሖዋ ያለ ማን ነው?
19 በዚህ ጊዜ ሚካያህ እንዲህ አለ፦ “እንግዲህ የይሖዋን ቃል ስማ፦ ይሖዋ በዙፋኑ ላይ ተቀምጦ+ የሰማያት ሠራዊትም ሁሉ በቀኙና በግራው አጠገቡ ቆመው+ አየሁ።