-
ኢዮብ 2:1-3አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
2 የእውነተኛው አምላክ ልጆች፣*+ በይሖዋ ፊት ለመቆም+ የሚገቡበት ቀን በደረሰ ጊዜ ሰይጣንም በይሖዋ ፊት ለመቆም እነሱ መካከል ገባ።+
2 ከዚያም ይሖዋ ሰይጣንን “ከየት መጣህ?” አለው። ሰይጣንም “በምድር ሁሉ ላይ ስዞርና በእሷ ላይ ስመላለስ ቆይቼ መጣሁ”+ ሲል ለይሖዋ መለሰ። 3 ይሖዋም ሰይጣንን እንዲህ አለው፦ “አገልጋዬን ኢዮብን ተመለከትከው?* በምድር ላይ እንደ እሱ ያለ ሰው የለም። በንጹሕ አቋም የሚመላለስ ቅን ሰው*+ እንዲሁም አምላክን የሚፈራና ከክፋት የራቀ ነው። ያለምንም ምክንያት እንዳጠፋው* እኔን ለማነሳሳት ብትሞክርም+ እንኳ አሁንም በንጹሕ አቋሙ እንደጸና ነው።”+
-