1 ሳሙኤል 1:10 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 10 እሷም በጣም ተማርራ* ነበር፤ ስቅስቅ ብላም እያለቀሰች ወደ ይሖዋ ትጸልይ ጀመር።+ ኢዮብ 10:1 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 10 “ሕይወቴን ተጸየፍኳት።*+ አንዳች ሳላስቀር ብሶቴን አሰማለሁ። በታላቅ ምሬት* እናገራለሁ! ምሳሌ 14:10 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 10 ልብ የራሱን* ምሬት ያውቃል፤ደስታውንም ሌላ ሰው ሊጋራው አይችልም።