ዘፍጥረት 27:46 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 46 ከዚያ በኋላ ርብቃ ይስሐቅን እንዲህ ትለው ጀመር፦ “በሄት ሴቶች ልጆች የተነሳ ሕይወቴን ጠልቻለሁ።+ ያዕቆብም በዚህ አገር የሚገኙትን እንደነዚህ ያሉትን የሄት ሴቶች ልጆች የሚያገባ ከሆነ በሕይወት መኖር ለእኔ ምን ያደርግልኛል?”+ 1 ነገሥት 19:4 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 4 ከዚያም በምድረ በዳው የአንድ ቀን መንገድ ከተጓዘ በኋላ ወደ አንድ የክትክታ ዛፍ ሲደርስ ሥሩ ተቀመጠ፤ እንዲሞትም* መለመን ጀመረ። እንዲህም አለ፦ “አሁንስ በቅቶኛል! ይሖዋ ሆይ፣ እኔ ከአባቶቼ አልበልጥምና ሕይወቴን* ውሰዳት።”+ ኢዮብ 10:1 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 10 “ሕይወቴን ተጸየፍኳት።*+ አንዳች ሳላስቀር ብሶቴን አሰማለሁ። በታላቅ ምሬት* እናገራለሁ! ዮናስ 4:3 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 3 አሁንም ይሖዋ ሆይ፣ በሕይወት ከመኖር ይልቅ መሞት ስለሚሻለኝ እባክህ ግደለኝ።”*+
46 ከዚያ በኋላ ርብቃ ይስሐቅን እንዲህ ትለው ጀመር፦ “በሄት ሴቶች ልጆች የተነሳ ሕይወቴን ጠልቻለሁ።+ ያዕቆብም በዚህ አገር የሚገኙትን እንደነዚህ ያሉትን የሄት ሴቶች ልጆች የሚያገባ ከሆነ በሕይወት መኖር ለእኔ ምን ያደርግልኛል?”+
4 ከዚያም በምድረ በዳው የአንድ ቀን መንገድ ከተጓዘ በኋላ ወደ አንድ የክትክታ ዛፍ ሲደርስ ሥሩ ተቀመጠ፤ እንዲሞትም* መለመን ጀመረ። እንዲህም አለ፦ “አሁንስ በቅቶኛል! ይሖዋ ሆይ፣ እኔ ከአባቶቼ አልበልጥምና ሕይወቴን* ውሰዳት።”+