መዝሙር 89:14 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 14 ጽድቅና ፍትሕ የዙፋንህ መሠረት ናቸው፤+ታማኝ ፍቅርና ታማኝነት በፊትህ ናቸው።+ 1 ጴጥሮስ 2:23 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 23 ሲሰድቡት+ መልሶ አልተሳደበም።+ መከራ ሲደርስበት+ አልዛተም፤ ከዚህ ይልቅ በጽድቅ ለሚፈርደው ራሱን በአደራ ሰጠ።+