መዝሙር 37:23, 24 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 23 ይሖዋ በሰው መንገድ ደስ ሲሰኝ፣+አካሄዱን ይመራለታል።*+ 24 ቢወድቅም እንኳ አይዘረርም፤+ይሖዋ እጁን ይዞ* ይደግፈዋልና።+ መዝሙር 62:2 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 2 በእርግጥም እሱ ዓለቴና አዳኜ እንዲሁም አስተማማኝ መጠጊያዬ ነው፤+ከልክ በላይ አልናወጥም።+ መዝሙር 121:3 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 3 እሱ እግርህ እንዲንሸራተት* ፈጽሞ አይፈቅድም።+ ጠባቂህ በጭራሽ አያንቀላፋም።