የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ዘፍጥረት 4:9, 10
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 9 በኋላም ይሖዋ ቃየንን “ወንድምህ አቤል የት ነው?” አለው፤ እሱም “እኔ አላውቅም። እኔ የወንድሜ ጠባቂ ነኝ?” አለ። 10 በዚህ ጊዜ እንዲህ አለው፦ “ያደረግከው ነገር ምንድን ነው? ስማ! የወንድምህ ደም ከምድር ወደ እኔ እየጮኸ ነው።+

  • ዘፍጥረት 9:5
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 5 ከዚህም በተጨማሪ ሕይወታችሁ የሆነውን ደማችሁን* የሚያፈሰውን ሁሉ ተጠያቂ አደርገዋለሁ። እያንዳንዱን ሕያው ፍጡር ተጠያቂ አደርገዋለሁ፤ እያንዳንዱንም ሰው ለወንድሙ ሕይወት ተጠያቂ አደርገዋለሁ።+

  • ዘዳግም 32:43
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 43 እናንተ ብሔራት ከሕዝቡ ጋር ደስ ይበላችሁ፤+

      እሱ የአገልጋዮቹን ደም ይመልሳልና፤+

      ተቃዋሚዎቹንም ይበቀላል፤+

      ለሕዝቡም ምድር ያስተሰርይለታል።”*

  • 2 ነገሥት 9:24
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 24 ኢዩም ቀስቱን አስፈንጥሮ ኢዮራምን በትከሻዎቹ መካከል ወጋው፤ ቀስቱም በልቡ በኩል ወጣ፤ ኢዮራምም እዚያው ጦር ሠረገላው ውስጥ ወደቀ።

  • 2 ነገሥት 9:26
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 26 ‘“ትናንት የናቡቴን ደምና የልጆቹን ደም እንዳየሁ ሁሉ”+ ይላል ይሖዋ፣ “በዚህ የእርሻ ቦታ ላይ ዋጋህን እከፍልሃለሁ”+ ይላል ይሖዋ።’ በመሆኑም ይሖዋ በተናገረው ቃል መሠረት አንስተህ እርሻው ላይ ጣለው።”+

  • 2 ነገሥት 24:3, 4
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 3 ይህ ነገር ይሖዋ ባዘዘው መሠረት በይሁዳ ላይ የደረሰው ይሁዳን ከፊቱ ለማጥፋት ነው፤+ ይህም የሆነው ምናሴ በሠራቸው ኃጢአቶች ሁሉ የተነሳ ነው፤+ 4 ንጹሕ ደም በማፍሰስ ኢየሩሳሌም በንጹሕ ደም እንድትጥለቀለቅ በማድረጉ ነው፤+ ይሖዋም ይቅር ለማለት ፈቃደኛ አልሆነም።+

  • ሉቃስ 11:49-51
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 49 ስለዚህ የአምላክ ጥበብ እንዲህ አለች፦ ‘ነቢያትንና ሐዋርያትን ወደ እነሱ እልካለሁ፤ እነሱም አንዳንዶቹን ይገድላሉ በአንዳንዶቹም ላይ ስደት ያደርሳሉ፤ 50 በመሆኑም ይህ ትውልድ ዓለም ከተመሠረተበት* ጊዜ ጀምሮ ለፈሰሰው የነቢያት ደም ሁሉ ተጠያቂ ነው፤*+ 51 ከአቤል+ አንስቶ በመሠዊያውና በቤቱ* መካከል እስከተገደለው እስከ ዘካርያስ+ ድረስ ለፈሰሰው ደም ተጠያቂ ነው።’ አዎ፣ እላችኋለሁ፣ ይህ ትውልድ ይጠየቅበታል።*

የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ ጽሑፎች (2011-2025)
ውጣ
ግባ
  • የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ