15 ታቦቱን የተሸከሙት ካህናት ዮርዳኖስ ጋ ሲደርሱና እግራቸውን ውኃው ዳር ሲያጠልቁ (ወቅቱ መከር ስለነበር በመከር ጊዜ እንደሚሆነው ሁሉ የዮርዳኖስ ወንዝ ሞልቶ ዳርቻውን አጥለቅልቆት ነበር)+ 16 ከላይ ይወርድ የነበረው ውኃ ቆመ። ውኃውም በሩቅ ይኸውም በጻረታን አጠገብ በምትገኘው በአዳም ከተማ እንደ ግድብ ተቆልሎ ቆመ፤ በአረባ ወደሚገኘው ባሕር ይኸውም ወደ ጨው ባሕር የሚወርደውም ውኃ ደረቀ። ውኃው ተቋርጦ ስለነበር ሕዝቡ ከኢያሪኮ ማዶ ወዳለው ስፍራ ተሻገረ።