-
መዝሙር 119:139አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
139 ጠላቶቼ ቃልህን ስለረሱ
ቅንዓቴ ይበላኛል።+
-
-
ዮሐንስ 2:13-17አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
13 በዚህ ጊዜ የአይሁዳውያን ፋሲካ*+ ቀርቦ ነበር፤ ኢየሱስም ወደ ኢየሩሳሌም ወጣ። 14 በቤተ መቅደሱ ውስጥ ከብት፣ በግና ርግብ+ የሚሸጡ ሰዎችን እንዲሁም በዚያ የተቀመጡ ገንዘብ መንዛሪዎችን አገኘ። 15 በዚህ ጊዜ የገመድ ጅራፍ ሠርቶ ሁሉንም ከበጎቻቸውና ከከብቶቻቸው ጋር አስወጣ፤ የገንዘብ ለዋጮችንም ሳንቲሞች በተነ፤ ጠረጴዛዎቻቸውንም ገለባበጠ።+ 16 ርግብ ሻጮቹንም “እነዚህን ከዚህ አስወጡ! የአባቴን ቤት የንግድ ቤት* ማድረጋችሁ ይብቃ!” አላቸው።+ 17 ደቀ መዛሙርቱም “ለቤትህ ያለኝ ቅንዓት ይበላኛል”+ ተብሎ የተጻፈው ትዝ አላቸው።
-