መዝሙር 25:9 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 9 የዋሆችን በትክክለኛ መንገድ* ይመራቸዋል፤+እንዲሁም ለየዋሆች መንገዱን ያስተምራል።+ መዝሙር 32:8 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 8 አንተ እንዲህ ብለሃል፦ “ጥልቅ ማስተዋል እሰጥሃለሁ፤ ልትሄድበት የሚገባውንም መንገድ አስተምርሃለሁ።+ ዓይኔን በአንተ ላይ አድርጌ እመክርሃለሁ።+ መዝሙር 37:23 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 23 ይሖዋ በሰው መንገድ ደስ ሲሰኝ፣+አካሄዱን ይመራለታል።*+ መዝሙር 143:10 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 10 አንተ አምላኬ ስለሆንክ፣ፈቃድህን እንድፈጽም አስተምረኝ።+ መንፈስህ ጥሩ ነው፤በደልዳላ መሬት* ይምራኝ። ምሳሌ 3:6 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 6 በመንገድህ ሁሉ እሱን ግምት ውስጥ አስገባ፤+እሱም ጎዳናህን ቀና ያደርገዋል።+