-
መዝሙር 81:11, 12አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
11 ሕዝቤ ግን ድምፄን አልሰማም፤
እስራኤል ለእኔ አይገዛም።+
-
-
ኤርምያስ 7:24-26አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
24 እነሱ ግን አልሰሙም ወይም ጆሯቸውን አልሰጡም፤+ ይልቁንም ግትር ሆነው ክፉ ልባቸውን በመከተል በገዛ ራሳቸው ዕቅድ* ሄዱ፤+ ወደ ፊት በመሄድ ፋንታ ወደ ኋላ ተመለሱ፤ 25 አባቶቻችሁ ከግብፅ ምድር ከወጡበት ጊዜ አንስቶ እስከዚህ ቀን ድረስ ይህን አደረጉ።+ በመሆኑም አገልጋዮቼ የሆኑትን ነቢያት ሁሉ ወደ እናንተ መላኬን ቀጠልኩ፤ ደግሜ ደጋግሜ በየዕለቱ* ላክኋቸው።+ 26 እነሱ ግን እኔን ለመስማት እንቢተኛ ሆኑ፤ ጆሯቸውንም አልሰጡም።+ ይልቁንም ግትር ሆኑ፤* አባቶቻቸው ከሠሩት የከፋ ነገር አደረጉ!
-