8 “አሁንም እናንተ እጅግ ብዙ ስለሆናችሁና ኢዮርብዓም አማልክት አድርጎ የሠራላችሁን የወርቅ ጥጃዎች+ ስለያዛችሁ በዳዊት ልጆች እጅ ያለውን የይሖዋን መንግሥት መቋቋም እንደምትችሉ ተሰምቷችኋል። 9 የአሮን ዘሮች የሆኑትን የይሖዋን ካህናትና ሌዋውያንን አላባረራችሁም?+ ደግሞስ እንደ ሌሎቹ አገሮች ሕዝቦች የራሳችሁን ካህናት አልሾማችሁም?+ አንድ ወይፈንና ሰባት አውራ በጎች ይዞ የሚመጣ ማንኛውም ሰው አማልክት ላልሆኑት ጣዖቶች ካህን መሆን ይችላል።