ዘዳግም 1:16, 17 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 16 “በዚያን ጊዜ ለዳኞቻችሁ ይህን መመሪያ ሰጠኋቸው፦ ‘በወንድሞቻችሁ መካከል የተፈጠረን አንድ ጉዳይ በምትሰሙበት ጊዜ በሰውየውና በወንድሙ ወይም በባዕድ አገሩ ሰው መካከል+ በጽድቅ ፍረዱ።+ 17 በምትፈርዱበት ጊዜ አታዳሉ።+ ትንሹንም ሆነ ትልቁን እኩል ስሙ።+ ፍርድ የአምላክ ስለሆነ+ ሰውን አትፍሩ፤+ አንድ ጉዳይ ከከበዳችሁ ወደ እኔ አምጡት፤ እኔም እሰማዋለሁ።’+ 2 ዜና መዋዕል 19:7 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 7 አሁንም ይሖዋን መፍራት በእናንተ ላይ ይሁን።+ በአምላካችን በይሖዋ ዘንድ ፍትሕ ማዛባት፣+ አድልዎ+ ወይም ጉቦ መቀበል+ ስለሌለ የምታደርጉትን ነገር በጥንቃቄ አከናውኑ።” ምሳሌ 18:5 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 5 ለክፉ ሰው ማድላት፣ጻድቁንም ፍትሕ መንፈግ+ መልካም አይደለም።+
16 “በዚያን ጊዜ ለዳኞቻችሁ ይህን መመሪያ ሰጠኋቸው፦ ‘በወንድሞቻችሁ መካከል የተፈጠረን አንድ ጉዳይ በምትሰሙበት ጊዜ በሰውየውና በወንድሙ ወይም በባዕድ አገሩ ሰው መካከል+ በጽድቅ ፍረዱ።+ 17 በምትፈርዱበት ጊዜ አታዳሉ።+ ትንሹንም ሆነ ትልቁን እኩል ስሙ።+ ፍርድ የአምላክ ስለሆነ+ ሰውን አትፍሩ፤+ አንድ ጉዳይ ከከበዳችሁ ወደ እኔ አምጡት፤ እኔም እሰማዋለሁ።’+
7 አሁንም ይሖዋን መፍራት በእናንተ ላይ ይሁን።+ በአምላካችን በይሖዋ ዘንድ ፍትሕ ማዛባት፣+ አድልዎ+ ወይም ጉቦ መቀበል+ ስለሌለ የምታደርጉትን ነገር በጥንቃቄ አከናውኑ።”