መዝሙር 144:5 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 5 ይሖዋ ሆይ፣ ሰማያትህን ወደ ታች ዝቅ አድርገህ* ውረድ፤+ተራሮችን ዳስሰህ እንዲጨሱ አድርግ።+ ናሆም 1:6 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 6 በቁጣው ፊት ማን ሊቆም ይችላል?+ የንዴቱን ትኩሳት ሊቋቋም የሚችልስ ማን ነው?+ ቁጣው እንደ እሳት ይፈስሳል፤ዓለቶችም ከእሱ የተነሳ ይፈረካከሳሉ።