መዝሙር 132:11 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 11 ይሖዋ ለዳዊት ምሏል፤የገባውን ቃል ፈጽሞ አያጥፍም፦ “ከዘሮችህ መካከል አንዱን*በዙፋንህ ላይ አስቀምጣለሁ።+ ሕዝቅኤል 34:23 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 23 በእነሱ ላይ አንድ እረኛ ይኸውም አገልጋዬን ዳዊትን* አስነሳለሁ፤+ እሱም ይመግባቸዋል። እሱ ራሱ ያሰማራቸዋል፤ እረኛቸውም ይሆናል።+ ሆሴዕ 3:5 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 5 ከዚያም በኋላ የእስራኤል ሕዝብ ተመልሰው አምላካቸውን ይሖዋንና ንጉሣቸውን ዳዊትን ይፈልጋሉ፤+ በዘመኑም መጨረሻ ወደ ይሖዋና ወደ ጥሩነቱ እየተንቀጠቀጡ ይመጣሉ።+ ዮሐንስ 7:42 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 42 ቅዱስ መጽሐፉ ክርስቶስ ከዳዊት ዘርና+ ዳዊት ከኖረበት መንደር+ ከቤተልሔም+ እንደሚመጣ ይናገር የለም?”
5 ከዚያም በኋላ የእስራኤል ሕዝብ ተመልሰው አምላካቸውን ይሖዋንና ንጉሣቸውን ዳዊትን ይፈልጋሉ፤+ በዘመኑም መጨረሻ ወደ ይሖዋና ወደ ጥሩነቱ እየተንቀጠቀጡ ይመጣሉ።+