1 ሳሙኤል 2:9 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 9 እሱ የታማኞቹን እርምጃ ይጠብቃል፤+ክፉዎች ግን በጨለማ ውስጥ ጸጥ እንዲሉ ይደረጋሉ፤+ሰው የበላይ የሚሆነው በኃይሉ አይደለምና።+ መዝሙር 37:24 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 24 ቢወድቅም እንኳ አይዘረርም፤+ይሖዋ እጁን ይዞ* ይደግፈዋልና።+ መዝሙር 121:3 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 3 እሱ እግርህ እንዲንሸራተት* ፈጽሞ አይፈቅድም።+ ጠባቂህ በጭራሽ አያንቀላፋም። ሰቆቃወ ኤርምያስ 3:22 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 22 ከይሖዋ ታማኝ ፍቅር የተነሳ ሙሉ በሙሉ አልጠፋንም፤+ምሕረቱ ፈጽሞ አያልቅምና።+