18 ይሁን እንጂ የማኅበረሰቡ አለቆች በእስራኤል አምላክ በይሖዋ ምለውላቸው+ ስለነበር እስራኤላውያን ጥቃት አልሰነዘሩባቸውም። ስለሆነም መላው ማኅበረሰብ በአለቆቹ ላይ ማጉረምረም ጀመረ። 19 በዚህ ጊዜ አለቆቹ በሙሉ መላውን ማኅበረሰብ እንዲህ አሉ፦ “በእስራኤል አምላክ በይሖዋ ስም ስለማልንላቸው ጉዳት ልናደርስባቸው አንችልም። 20 እንግዲህ የምናደርገው ነገር ቢኖር በማልንላቸው መሐላ የተነሳ ቁጣ እንዳይመጣብን በሕይወት እንዲኖሩ መተው ብቻ ነው።”+