6 ንጉሥ ዖዝያ በሞተበት ዓመት+ ይሖዋን በረጅምና ከፍ ባለ ዙፋን ላይ ተቀምጦ አየሁት፤+ የልብሱም ዘርፍ ቤተ መቅደሱን ሞልቶት ነበር። 2 ሱራፌልም ከእሱ በላይ ቆመው ነበር፤ እያንዳንዳቸውም ስድስት ክንፎች ነበሯቸው። እያንዳንዱ በሁለቱ ክንፍ ፊቱን ይሸፍን፣ በሁለቱ ክንፍ እግሩን ይሸፍን፣ በሁለቱ ክንፍ ደግሞ ይበር ነበር።
3 አንዳቸውም ሌላውን እንዲህ ይሉ ነበር፦
“የሠራዊት ጌታ ይሖዋ ቅዱስ፣ ቅዱስ፣ ቅዱስ ነው።+
መላዋ ምድር በክብሩ ተሞልታለች።”