ዘፍጥረት 12:7 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 7 ይሖዋም ለአብራም ተገለጠለትና “ይህችን ምድር ለዘርህ+ እሰጣለሁ”+ አለው። ስለዚህ አብራም ተገልጦለት ለነበረው ለይሖዋ በዚያ መሠዊያ ሠራ። ዘፍጥረት 15:13, 14 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 13 አምላክም አብራምን እንዲህ አለው፦ “ዘሮችህ በባዕድ አገር ባዕዳን ሆነው እንደሚኖሩ እንዲሁም በዚያ ያሉት ሰዎች ለ400 ዓመት በባርነት እንደሚገዟቸውና እንደሚያጎሳቁሏቸው በእርግጥ እወቅ።+ 14 ይሁንና በባርነት በሚገዛቸው ብሔር ላይ እፈርዳለሁ፤+ እነሱም ብዙ ንብረት ይዘው ይወጣሉ።+ ዘፀአት 2:24 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 24 ከጊዜ በኋላም አምላክ በመቃተት የሚያሰሙትን ጩኸት አዳመጠ፤+ እንዲሁም ከአብርሃም፣ ከይስሐቅና ከያዕቆብ ጋር የገባውን ቃል ኪዳኑን አሰበ።+ ዘዳግም 9:5 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 5 የእነሱን ምድር ገብተህ የምትወርሰው ከጽድቅህ ወይም ከልብህ ቅንነት የተነሳ አይደለም። ከዚህ ይልቅ አምላክህ ይሖዋ እነዚህን ብሔራት ከፊትህ የሚያባርራቸው ከራሳቸው ክፋት የተነሳ ነው፤+ እንዲሁም ይሖዋ ለአባቶችህ ለአብርሃም፣+ ለይስሐቅና+ ለያዕቆብ+ የማለላቸውን ቃል ለመፈጸም ሲል ነው።
13 አምላክም አብራምን እንዲህ አለው፦ “ዘሮችህ በባዕድ አገር ባዕዳን ሆነው እንደሚኖሩ እንዲሁም በዚያ ያሉት ሰዎች ለ400 ዓመት በባርነት እንደሚገዟቸውና እንደሚያጎሳቁሏቸው በእርግጥ እወቅ።+ 14 ይሁንና በባርነት በሚገዛቸው ብሔር ላይ እፈርዳለሁ፤+ እነሱም ብዙ ንብረት ይዘው ይወጣሉ።+
5 የእነሱን ምድር ገብተህ የምትወርሰው ከጽድቅህ ወይም ከልብህ ቅንነት የተነሳ አይደለም። ከዚህ ይልቅ አምላክህ ይሖዋ እነዚህን ብሔራት ከፊትህ የሚያባርራቸው ከራሳቸው ክፋት የተነሳ ነው፤+ እንዲሁም ይሖዋ ለአባቶችህ ለአብርሃም፣+ ለይስሐቅና+ ለያዕቆብ+ የማለላቸውን ቃል ለመፈጸም ሲል ነው።