ዘፀአት 17:2 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 2 በመሆኑም ሕዝቡ “የሚጠጣ ውኃ ስጠን” በማለት ከሙሴ ጋር ይጣላ ጀመር።+ ሙሴ ግን “ከእኔ ጋር የምትጣሉት ለምንድን ነው? ይሖዋንስ ለምን ትፈታተኑታላችሁ?”+ አላቸው። መዝሙር 78:18 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 18 እንዲሁም የተመኙትን* ምግብ እንዲሰጣቸው በመጠየቅአምላክን በልባቸው ተገዳደሩት።*+ 1 ቆሮንቶስ 10:9 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 9 ከእነሱ አንዳንዶቹ ይሖዋን* ተፈታትነው በእባቦች እንደጠፉ እኛም አንፈታተነው።+ ዕብራውያን 3:8, 9 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 8 በምድረ በዳ እጅግ የሚያስቆጣ ድርጊት በተፈጸመበት በፈተና ቀን እንደሆነው ልባችሁን አታደንድኑ፤+ 9 በዚያ፣ አባቶቻችሁ ያደረግኩትን ሁሉ ለ40 ዓመት ቢያዩም እኔን በመፈተን ተገዳደሩኝ።+
2 በመሆኑም ሕዝቡ “የሚጠጣ ውኃ ስጠን” በማለት ከሙሴ ጋር ይጣላ ጀመር።+ ሙሴ ግን “ከእኔ ጋር የምትጣሉት ለምንድን ነው? ይሖዋንስ ለምን ትፈታተኑታላችሁ?”+ አላቸው።
8 በምድረ በዳ እጅግ የሚያስቆጣ ድርጊት በተፈጸመበት በፈተና ቀን እንደሆነው ልባችሁን አታደንድኑ፤+ 9 በዚያ፣ አባቶቻችሁ ያደረግኩትን ሁሉ ለ40 ዓመት ቢያዩም እኔን በመፈተን ተገዳደሩኝ።+