-
መሳፍንት 6:1-5አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
6 እስራኤላውያን ግን እንደገና በይሖዋ ፊት መጥፎ ነገር አደረጉ፤+ በመሆኑም ይሖዋ ለሰባት ዓመት ለምድያማውያን አሳልፎ ሰጣቸው።+ 2 የምድያማውያን እጅ በእስራኤል ላይ በረታ።+ እስራኤላውያን በምድያማውያን የተነሳ በተራሮች ላይ፣ በዋሻዎች ውስጥና በቀላሉ በማይደረስባቸው ስፍራዎች ለመደበቂያ የሚሆኑ ቦታዎችን* ለራሳቸው አዘጋጁ።+ 3 እነሱም ዘር በሚዘሩበት ጊዜ ሁሉ ምድያማውያን፣ አማሌቃውያንና+ የምሥራቅ ሰዎች+ ጥቃት ይሰነዝሩባቸው ነበር። 4 እንዲሁም በዙሪያቸው በመስፈር እስከ ጋዛ ድረስ ያለውን የምድሩን ሰብል ያጠፉ ነበር፤ ለእስራኤላውያን የሚበሉት ምንም ነገር አያስተርፉላቸውም፤ በግም ሆነ ከብት ወይም አህያ አያስቀሩላቸውም ነበር።+ 5 ምክንያቱም ከብቶቻቸውንና ድንኳኖቻቸውን ይዘው እንደ አንበጣ መንጋ ብዙ ሆነው ይመጡ ነበር፤+ እነሱም ሆኑ ግመሎቻቸው ለቁጥር የሚያታክቱ ነበሩ፤+ ወደዚያም የሚመጡት ምድሪቱን ለማጥፋት ነበር።
-