13 ይወድሃል፣ ይባርክሃል እንዲሁም ያበዛሃል። አዎ፣ ለአንተ ሊሰጥህ ለአባቶችህ በማለላቸው ምድር ላይ የሆድህን ፍሬ፣+ የመሬትህን ምርት፣ እህልህን፣ አዲሱን የወይን ጠጅህን፣ ዘይትህን፣+ የከብቶችህን ጥጆችና የመንጋህን ግልገሎች ይባርክልሃል።+ 14 አንተም ከሕዝቦች ሁሉ ይበልጥ የተባረክ ትሆናለህ፤+ በመካከልህ ልጅ የሌለው ወንድ ወይም ሴት አይገኝም፤ እንስሶችህም ግልገል የሌላቸው አይሆኑም።+