7 ልቤ ጽኑ ነው፤
አምላክ ሆይ፣ ልቤ ጽኑ ነው።+
እዘምራለሁ፤ ደግሞም አዜማለሁ።
8 ልቤ ሆይ፣ ተነሳ።
ባለ አውታር መሣሪያ ሆይ፣ አንተም በገና ሆይ፣ ተነሱ።
እኔም በማለዳ እነሳለሁ።+
9 ይሖዋ ሆይ፣ በሕዝቦች መካከል አወድስሃለሁ፤+
በብሔራት መካከል የውዳሴ መዝሙር እዘምርልሃለሁ።+
10 ታማኝ ፍቅርህ ታላቅ ነውና፤ እንደ ሰማያት ከፍ ያለ ነው፤+
ታማኝነትህም እስከ ደመናት ድረስ ነው።
11 አምላክ ሆይ፣ ከሰማያት በላይ ከፍ ከፍ በል፤
ክብርህ በምድር ሁሉ ላይ ይሁን።+