-
የሐዋርያት ሥራ 1:16-20አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
16 “ወንድሞች፣ ኢየሱስን የያዙትን ሰዎች እየመራ ስላመጣው ስለ ይሁዳ+ መንፈስ ቅዱስ በዳዊት በኩል በትንቢት የተናገረው የቅዱስ መጽሐፉ ቃል መፈጸሙ የግድ ነበር።+ 17 ምክንያቱም እሱ ከእኛ እንደ አንዱ ተቆጥሮ የነበረ+ ከመሆኑም በላይ በዚህ አገልግሎት የመካፈል አጋጣሚ አግኝቶ ነበር። 18 (ይኸው ሰው ለዓመፅ ሥራው በተከፈለው ደሞዝ+ መሬት ገዛ፤ በአናቱም ወድቆ ሰውነቱ ፈነዳ፤* ሆድ ዕቃውም ተዘረገፈ።+ 19 ይህም በኢየሩሳሌም ነዋሪዎች ሁሉ ዘንድ ታወቀ፤ በመሆኑም መሬቱ በቋንቋቸው አኬልዳማ ተብሎ ተጠራ፤ ትርጉሙም “የደም መሬት” ማለት ነው።) 20 በመዝሙር መጽሐፍ ላይ ‘መኖሪያው ወና ይሁን፤ በውስጡም ማንም ሰው አይኑርበት’+ እንዲሁም ‘የበላይ ተመልካችነት ሹመቱን ሌላ ሰው ይውሰደው’ ተብሎ ተጽፏልና።+
-