የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ማቴዎስ 22:43, 44
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 43 እሱም እንዲህ ሲል ጠየቃቸው፦ “ታዲያ ዳዊት በመንፈስ ተመርቶ+ እንዴት ጌታ ብሎ ይጠራዋል? 44 ምክንያቱም ዳዊት ‘ይሖዋ* ጌታዬን፦ “ጠላቶችህን ከእግርህ በታች እስካደርግልህ ድረስ በቀኜ ተቀመጥ” አለው’ ሲል ተናግሯል።+

  • ማርቆስ 12:36
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 36 ዳዊት ራሱ በመንፈስ ቅዱስ+ ሲናገር ‘ይሖዋ* ጌታዬን “ጠላቶችህን ከእግርህ በታች እስካደርግልህ ድረስ በቀኜ ተቀመጥ” አለው’ ብሏል።+

  • ሉቃስ 20:42, 43
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 42 ምክንያቱም ዳዊት ራሱ በመዝሙር መጽሐፍ ላይ እንዲህ ብሏል፦ ‘ይሖዋ* ጌታዬን እንዲህ ብሎታል፦ “በቀኜ ተቀመጥ፤ 43 ጠላቶችህን ለእግርህ መርገጫ እስከማደርግልህ ድረስ በቀኜ ሁን።”’+

  • የሐዋርያት ሥራ 2:34, 35
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 34 ዳዊት ወደ ሰማያት አልወጣምና፤ ሆኖም እሱ ራሱ እንዲህ ሲል ተናግሯል፦ ‘ይሖዋ* ጌታዬን እንዲህ ብሎታል፦ “በቀኜ ተቀመጥ፤ 35 ጠላቶችህን ለእግርህ መርገጫ እስከማደርግልህ ድረስ በቀኜ ሁን።”’+

  • 1 ቆሮንቶስ 15:25
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 25 አምላክ ጠላቶችን ሁሉ ከእግሩ በታች እስኪያደርግለት ድረስ ንጉሥ ሆኖ ሊገዛ ይገባዋልና።+

  • ዕብራውያን 1:3
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 3 እሱ የአምላክ ክብር+ ነጸብራቅና የማንነቱ ትክክለኛ አምሳያ ነው፤+ እሱም በኃያል ቃሉ ሁሉንም ነገር ደግፎ ያኖራል። እኛን ከኃጢአታችን ካነጻ+ በኋላም በሰማይ በግርማዊው ቀኝ ተቀምጧል።+

  • ዕብራውያን 1:13
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 13 ይሁንና “ጠላቶችህን ለእግርህ መርገጫ እስከማደርግልህ ድረስ በቀኜ ተቀመጥ”+ ብሎ ከመላእክት መካከል ስለ የትኛው መልአክ ተናግሮ ያውቃል?

  • ዕብራውያን 10:12, 13
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 12 ይህ ሰው ግን ስለ ኃጢአት ለሁልጊዜ የሚሆን አንድ መሥዋዕት አቅርቦ በአምላክ ቀኝ ተቀምጧል፤+ 13 ከዚያን ጊዜ አንስቶ ጠላቶቹ የእግሩ መርገጫ እስኪደረጉ ድረስ በመጠባበቅ ላይ ይገኛል።+

የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ ጽሑፎች (2011-2025)
ውጣ
ግባ
  • የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ