31 ‘ታላቅ ጩኸት እስከ ምድር ዳርቻ ድረስ ያስተጋባል፤
ይሖዋ ከብሔራት ጋር ሙግት አለውና።
እሱ ራሱ በሰዎች ሁሉ ላይ ይፈርዳል።+
ክፉዎችንም ለሰይፍ ይዳርጋል’ ይላል ይሖዋ።
32 የሠራዊት ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦
‘እነሆ፣ ጥፋት ብሔራትን አንድ በአንድ ያዳርሳል፤+
ታላቅ አውሎ ነፋስም ከምድር ዳርቻዎች ይነሳል።+
33 “‘በዚያም ቀን፣ ይሖዋ የገደላቸው ከምድር ዳር እስከ ምድር ዳር ድረስ ይሆናሉ። አይለቀስላቸውም፣ አይሰበሰቡም ወይም አይቀበሩም። በምድር ላይ እንደ ፍግ ይሆናሉ።’