-
ኢያሱ 4:5-7አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
5 ኢያሱም እንዲህ አላቸው፦ “የአምላካችሁን የይሖዋን ታቦት ቀድማችሁ ወደ ዮርዳኖስ መሃል ሂዱ፤ እያንዳንዳችሁም በእስራኤላውያን ነገዶች ቁጥር ልክ አንድ አንድ ድንጋይ አንስታችሁ በትከሻችሁ ተሸከሙ፤ 6 ይህም በመካከላችሁ እንደ ምልክት ሆኖ ያገለግላል። ምናልባት ወደፊት ልጆቻችሁ* ‘እነዚህን ድንጋዮች እዚህ ያስቀመጣችኋቸው ለምንድን ነው?’ ብለው ቢጠይቋችሁ+ 7 እንዲህ በሏቸው፦ ‘የዮርዳኖስ ውኃ በይሖዋ የቃል ኪዳን ታቦት ፊት ተቋርጦ ስለነበር ነው።+ ታቦቱ ዮርዳኖስን ሲሻገር የዮርዳኖስ ውኃ ተቋረጠ። እነዚህ ድንጋዮች ለእስራኤላውያን በዘላቂነት እንደ መታሰቢያ* ሆነው ያገለግላሉ።’”+
-