-
ዕብራውያን 12:9-11አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
9 ከዚህም በላይ ሰብዓዊ አባቶቻችን ይገሥጹን ነበር፤ እኛም እናከብራቸው ነበር። ታዲያ የመንፈሳዊ ሕይወታችን አባት ለሆነው ይበልጥ በፈቃደኝነት በመገዛት በሕይወት ልንኖር አይገባም?+ 10 እነሱ መልካም መስሎ በታያቸው መንገድ ለጥቂት ጊዜ ገሥጸውናል፤ እሱ ግን ከቅድስናው ተካፋዮች እንድንሆን+ ለጥቅማችን ሲል ይገሥጸናል። 11 እርግጥ ነው፣ ማንኛውም ተግሣጽ ለጊዜው የሚያስደስት አይመስልም፤ ይልቁንም ያስከፋል፤* በኋላ ግን በተግሣጽ ሥልጠና ላገኙ ሰዎች የጽድቅን ሰላማዊ ፍሬ ያፈራላቸዋል።
-