-
ዘፀአት 7:20አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
20 ሙሴና አሮን ወዲያውኑ ልክ ይሖዋ እንዳዘዛቸው አደረጉ። እሱም ፈርዖንና አገልጋዮቹ እያዩ በትሩን አንስቶ በአባይ ወንዝ ውስጥ ያለውን ውኃ መታ፤ በወንዙ ውስጥ የነበረውም ውኃ በሙሉ ወደ ደም ተለወጠ።+
-
-
ዘፀአት 8:6አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
6 ስለዚህ አሮን በግብፅ ውኃዎች ላይ እጁን ሰነዘረ፤ እንቁራሪቶቹም እየወጡ የግብፅን ምድር መውረር ጀመሩ።
-
-
ዘፀአት 8:17አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
17 እነሱም እንዲሁ አደረጉ። አሮን በእጁ የያዘውን በትር ሰንዝሮ የምድርን አቧራ መታ፤ ትንኞቹም ሰዉንም እንስሳውንም ወረሩ። በምድሪቱ ያለው አቧራ ሁሉ በመላው የግብፅ ምድር ላይ ትንኝ ሆነ።+
-
-
ዘፀአት 9:6አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
6 ይሖዋም በማግስቱ ይህን አደረገ፤ የግብፅ ከብት ሁሉ ይሞት ጀመር፤+ ከእስራኤላውያን ከብቶች መካከል ግን አንድ እንኳ አልሞተም።
-
-
ዘፀአት 9:10አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
10 እነሱም ከሸክላ መተኮሻ ምድጃ ጥቀርሻ ወስደው ፈርዖን ፊት ቆሙ፤ ሙሴም ጥቀርሻውን ወደ ሰማይ በተነው፤ ጥቀርሻውም በሰውና በእንስሳ ላይ መግል የያዘ እባጭ ሆኖ ወጣ።
-
-
ዘፀአት 9:23አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
23 በመሆኑም ሙሴ በትሩን ወደ ሰማይ አነሳ፤ ይሖዋም ነጎድጓድና በረዶ ላከ፤ እሳትም* በምድር ላይ ወረደ፤ ይሖዋ በግብፅ ምድር ላይ ያለማቋረጥ በረዶ እንዲወርድ አደረገ።
-
-
ዘፀአት 10:12አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
12 በዚህ ጊዜ ይሖዋ ሙሴን እንዲህ አለው፦ “አንበጦች መጥተው የግብፅን ምድር እንዲወሩና ከበረዶ የተረፈውን በምድሩ ላይ ያለውን ማንኛውንም ተክል ጠራርገው እንዲበሉ በግብፅ ምድር ላይ እጅህን ዘርጋ።”
-
-
ዘፀአት 10:21አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
21 ከዚያም ይሖዋ ሙሴን “በግብፅ ምድር ላይ ጨለማ ይኸውም የሚዳሰስ የሚመስል ድቅድቅ ጨለማ እንዲከሰት እጅህን ወደ ሰማይ ዘርጋ” አለው።
-