የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ኤርምያስ 49:7
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 7 የሠራዊት ጌታ ይሖዋ ስለ ኤዶም እንዲህ ይላል፦

      “ጥበብ ከቴማን+ ጠፍቷል?

      ጥሩ ምክርስ ከአስተዋዮች ጠፍቷል?

      ጥበባቸውስ ተበላሽቷል?

  • ሰቆቃወ ኤርምያስ 4:22
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 22 የጽዮን ሴት ልጅ ሆይ፣ በበደልሽ ምክንያት የደረሰብሽ ቅጣት አብቅቷል።

      ከእንግዲህ ወዲህ ወደ ግዞት አይወስድሽም።+

      ይሁንና የኤዶም ሴት ልጅ ሆይ፣ ትኩረቱን በሠራሽው በደል ላይ ያደርጋል።

      ኃጢአትሽን ይገልጣል።+

  • ሕዝቅኤል 25:12
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 12 “ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘ኤዶም በቂም በቀል ተነሳስቶ በይሁዳ ቤት ላይ እርምጃ ወስዷል፤ ደግሞም እነሱን በመበቀል ከፍተኛ በደል ፈጽሟል፤+

  • አብድዩ 10-13
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 10 በወንድምህ በያዕቆብ ላይ በተፈጸመው ግፍ የተነሳ+

      ኀፍረት ትከናነባለህ፤+

      ለዘላለምም ትጠፋለህ።+

      11 ዳር ቆመህ ትመለከት በነበረበት ጊዜ፣

      እንግዶች ሠራዊቱን ማርከው በወሰዱበትና+

      የባዕድ አገር ሰዎች በበሩ ገብተው በኢየሩሳሌም ላይ ዕጣ በተጣጣሉበት ጊዜ፣+

      አንተም ልክ እንደ እነሱ አደረግክ።

      12 በወንድምህ ቀን ይኸውም ወንድምህ ክፉ ነገር በደረሰበት ቀን መፈንደቅ አይገባህም ነበር፤+

      የይሁዳ ሕዝብ በጠፋበት ቀን ሐሴት ማድረግ አልነበረብህም፤+

      ደግሞም በጭንቀታቸው ቀን በእብሪት መናገር አይገባህም ነበር።

      13 በጥፋታቸው ቀን ወደ ሕዝቤ በር መምጣት አልነበረብህም፤+

      በጥፋቱ ቀን በደረሰበት መከራ መፈንደቅ አይገባህም ነበር፤

      ደግሞም ጥፋት በደረሰበት ቀን ሀብቱን መውሰድ አልነበረብህም።+

የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ ጽሑፎች (2011-2025)
ውጣ
ግባ
  • የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ