2 ነገሥት 19:35 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 35 በዚያም ሌሊት የይሖዋ መልአክ ወጥቶ በአሦራውያን ሰፈር የነበሩትን 185,000 ሰዎች ገደለ።+ ሰዎችም በማለዳ ሲነሱ ሬሳውን አዩ።+ ዳንኤል 6:22 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 22 አምላኬ መልአኩን ልኮ የአንበሶቹን አፍ ዘጋ፤+ እነሱም አልጎዱኝም፤+ በፊቱ ንጹሕ ሆኜ ተገኝቻለሁና፤ ንጉሥ ሆይ፣ በአንተም ላይ የሠራሁት በደል የለም።” የሐዋርያት ሥራ 5:18, 19 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 18 ሐዋርያትንም ይዘው እስር ቤት ከተቷቸው።+ 19 ይሁን እንጂ ሌሊት የይሖዋ* መልአክ የእስር ቤቱን በሮች ከፍቶ+ አወጣቸውና እንዲህ አላቸው፦ የሐዋርያት ሥራ 12:11 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 11 ጴጥሮስም የሆነውን ነገር ሲረዳ “ይሖዋ* መልአኩን ልኮ ከሄሮድስ እጅና አይሁዳውያን በእኔ ላይ ይደርሳል ብለው ካሰቡት ነገር ሁሉ እንደታደገኝ አሁን በእርግጥ አወቅኩ” አለ።+
11 ጴጥሮስም የሆነውን ነገር ሲረዳ “ይሖዋ* መልአኩን ልኮ ከሄሮድስ እጅና አይሁዳውያን በእኔ ላይ ይደርሳል ብለው ካሰቡት ነገር ሁሉ እንደታደገኝ አሁን በእርግጥ አወቅኩ” አለ።+