መዝሙር 26:1 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 26 ይሖዋ ሆይ፣ በንጹሕ አቋም* ተመላልሻለሁና ፍረድልኝ፤+ያለምንም ማወላወል በይሖዋ ታምኛለሁ።+ መዝሙር 96:13 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 13 እሱ እየመጣ ነውና፤*በምድር ላይ ለመፍረድ እየመጣ ነው። በዓለም* ላይ በጽድቅ፣በሕዝቦችም ላይ በታማኝነት ይፈርዳል።+