-
የሐዋርያት ሥራ 4:25-28አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
25 በመንፈስ ቅዱስ አማካኝነት በአገልጋይህ በአባታችን በዳዊት አፍ እንዲህ ብለሃል፦+ ‘ብሔራት ለምን ታወኩ? ሕዝቦችስ ለምን ከንቱ ነገር ያውጠነጥናሉ? 26 የምድር ነገሥታት ተሰለፉ፤ ገዢዎችም በአንድነት ተሰብስበው በይሖዋና* እሱ በቀባው* ላይ ተነሱ።’+ 27 በእርግጥም ሄሮድስና ጳንጥዮስ ጲላጦስ+ ከአሕዛብና ከእስራኤል ሕዝብ ጋር በዚህች ከተማ ተሰብስበው አንተ በቀባኸው+ በቅዱስ አገልጋይህ በኢየሱስ ላይ ተነሱ፤ 28 ይህም የሆነው እጅህና ፈቃድህ አስቀድመው የወሰኑት እንዲፈጸም ነው።+
-