-
መዝሙር 36:1አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
36 ኃጢአት፣ ክፉውን ሰው በልቡ ውስጥ ሆኖ ያናግረዋል፤
በዓይኖቹ ፊት አምላክን መፍራት የሚባል ነገር የለም።+
-
-
መዝሙር 36:4አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
4 በአልጋው ላይ ሆኖ እንኳ ክፋትን ያውጠነጥናል።
ጥሩ ባልሆነ መንገድ ላይ ይቆማል፤
መጥፎ የሆነውን ነገር ገሸሽ አያደርግም።
-
-
ሚክያስ 2:1አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
2 “መጥፎ ነገር ለሚሸርቡና
በአልጋቸው ላይ ሆነው ክፉ ነገር ለሚያውጠነጥኑ ወዮላቸው!
ጠዋት ሲነጋ ያሰቡትን ይፈጽማሉ፤
ምክንያቱም ይህን የሚያደርጉበት ኃይል በእጃቸው ነው።+
-