1 ሳሙኤል 3:12, 13 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 12 በዚያ ቀን ስለ ኤሊ ቤት የተናገርኩትን ነገር ሁሉ ከመጀመሪያ እስከ መጨረሻ በእሱ ላይ እፈጽማለሁ።+ 13 እሱ በሚያውቀው ጥፋት የተነሳ በቤቱ ላይ ለዘለቄታው እንደምፈርድ ንገረው፤+ ምክንያቱም ልጆቹ አምላክን ረግመዋል፤+ እሱ ግን አልገሠጻቸውም።+ 1 ነገሥት 1:5, 6 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 5 በዚህ ጊዜ የሃጊት ልጅ አዶንያስ+ “ንጉሥ እሆናለሁ!” በማለት ራሱን ከፍ ከፍ ያደርግ ጀመር። ለራሱም ሠረገላ ከነፈረሰኞቹ እንዲሁም ከፊት ከፊቱ የሚሮጡ 50 ሰዎች እንዲዘጋጁለት አደረገ።+ 6 አባቱ ግን አንድም ቀን “ይህን ያደረግከው ለምንድን ነው?” በማለት ተቃውሞት* አያውቅም ነበር። በተጨማሪም አዶንያስ እጅግ መልከ መልካም ነበር፤ እናቱ እሱን የወለደችው ከአቢሴሎም በኋላ ነበር። ምሳሌ 29:15 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 15 በትርና* ወቀሳ ጥበብ ያስገኛሉ፤+መረን የተለቀቀ ልጅ ግን እናቱን ያሳፍራል።
12 በዚያ ቀን ስለ ኤሊ ቤት የተናገርኩትን ነገር ሁሉ ከመጀመሪያ እስከ መጨረሻ በእሱ ላይ እፈጽማለሁ።+ 13 እሱ በሚያውቀው ጥፋት የተነሳ በቤቱ ላይ ለዘለቄታው እንደምፈርድ ንገረው፤+ ምክንያቱም ልጆቹ አምላክን ረግመዋል፤+ እሱ ግን አልገሠጻቸውም።+
5 በዚህ ጊዜ የሃጊት ልጅ አዶንያስ+ “ንጉሥ እሆናለሁ!” በማለት ራሱን ከፍ ከፍ ያደርግ ጀመር። ለራሱም ሠረገላ ከነፈረሰኞቹ እንዲሁም ከፊት ከፊቱ የሚሮጡ 50 ሰዎች እንዲዘጋጁለት አደረገ።+ 6 አባቱ ግን አንድም ቀን “ይህን ያደረግከው ለምንድን ነው?” በማለት ተቃውሞት* አያውቅም ነበር። በተጨማሪም አዶንያስ እጅግ መልከ መልካም ነበር፤ እናቱ እሱን የወለደችው ከአቢሴሎም በኋላ ነበር።