-
2 ሳሙኤል 15:2-4አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
2 አቢሴሎምም በጠዋት ተነስቶ ወደ ከተማዋ በር+ በሚወስደው መንገድ ዳር ይቆም ነበር። ማንም ሰው ሙግት ኖሮት ፍርድ ለማግኘት+ ወደ ንጉሡ በሚመጣበት ጊዜ አቢሴሎም ይጠራውና “ለመሆኑ አንተ የየትኛው ከተማ ሰው ነህ?” ይለው ነበር፤ እሱም “አገልጋይህ ከእስራኤል ነገዶች መካከል ከአንዱ ነው” ይለዋል። 3 አቢሴሎምም “አቤቱታህ ትክክልና ተገቢ ነው፤ ግን ምን ያደርጋል፣ ከንጉሡ ዘንድ ጉዳይህን የሚሰማልህ አንድም ሰው አታገኝም” ይለው ነበር። 4 ከዚያም አቢሴሎም “ምነው በምድሪቱ ላይ ዳኛ ሆኜ በተሾምኩ! ሙግት ያለው ወይም ፍርድ የሚፈልግ ማንኛውም ሰው ወደ እኔ መጥቶ ፍትሕ ማግኘት ይችል ነበር” ይል ነበር።
-