-
2 ሳሙኤል 19:25-27አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
25 እሱም ንጉሡን ለማግኘት ወደ ኢየሩሳሌም* በመጣ ጊዜ ንጉሡ “ሜፊቦስቴ፣ አብረኸኝ ያልሄድከው ለምንድን ነው?” አለው። 26 በዚህ ጊዜ እንዲህ አለው፦ “ጌታዬ ንጉሥ ሆይ፣ አገልጋዬ+ አታለለኝ። እኔ አገልጋይህ ሽባ+ ስለሆንኩ ‘በአህያዬ ላይ ተቀምጬ ከንጉሡ ጋር እንድሄድ አህያዬን ጫኑልኝ’ ብዬ ነበር። 27 ሆኖም እሱ በጌታዬ በንጉሡ ፊት የእኔን የአገልጋይህን ስም አጥፍቷል።+ ይሁን እንጂ ጌታዬ ንጉሡ እንደ እውነተኛው አምላክ መልአክ ስለሆነ መልካም መስሎ የታየህን አድርግ።
-
-
ምሳሌ 25:8አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
8 ክስ ለመመሥረት አትቸኩል፤
የኋላ ኋላ ባልንጀራህ ቢያዋርድህ ምን ይውጥሃል?+
-